20 የኩላሊት በሽታ መንሥኤዎች (Causes of Kidney Disease)

የኩላሊት በሽታ መንሥኤዎች
l

Tinsae Zelalem

ጤና ይስጥልኝ የላይፍ አስ ኤምዲ (Life as MD) ብሎግ ተከታታዮቻችን ዛሬ ስለ የኩላሊት በሽታ መንሥኤዎች እናወራለን።

ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች መጠናቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም ጎጂ ኬሚካሎች ከሰውነታችን ተጣርቶ እንዲወጣ የሚያደርግ የሰውነት ክፍል ነው። ስለዚህም ኩላሊት ላይ የሚደርስ ማንኛውም የሆነ ጉዳት ከፍተኛ የጤና መቃወስ ሊያስከትል ይችላል።

ከዚህ በፊት ባለው ፁሁፋችን ላይ እንደገለፅነው የኩላሊት ጉዳት አጣዳፊ እና የቆየ በሚል በሁለት ልንከፍለው እንችላለን። የበሽታው እድሜ ከ 3 ወር በታች ከሆነ አጣዳፊ የኩላሊት በሽታ ሲሆን ከ 3 ወር በላይ ከቆየ ደግሞ የቆየ የኩላሊት በሽታ በማለት እንጠራዋለን።

የኩላሊት በሽታ መንስኤዎች

አጣዳፊ የኩላሊት በሽታ መንሥኤዎች

1. ከተለመደው የደም ዝውውር መጠን  ያነሰ ደም ወደ ኩላሊት መፍሰስ

የደም መጠንን የሚቀንሱ ማንኛውም ችግሮች የኩላሊት መጎዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ምክንያቱም ኩላሊት ስራውን በትክክል እንዲሰራ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮች እና ኦክስጂን ያስፈልገዋል። ይህም ከ 40 እስከ 80% ለአጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት መንሥኤ ይሆናል፡፡

በደም እጥረት የሚከሰተው የኩላሊት መጎዳት ተገቢው ሕክምና በጊዜ ከተደረገለት በቀላሉ ሊድን ይችላል።

የደም ዝውውር መጠንን የሚቀንሱ ነገሮች ምንድናቸው?

 • በማንኛውም ምክንያት የሚከሰት የደም መፍሰስ ይህም በአደጋ የሚፈጠር ሊሆን ይችላል ወይም ከእርግዝና እና ወሊድ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሊሆን ይችላል። እንዲሁም በቀዶ ጥገና ጊዜ የሚያጋጥም ሊሆን ይችላል።
 • ሌላው እንደ ተቅማጥ፣ ትውከት እና የቃጠሎ አደጋ ያሉ በደም ውስጥ ያለው የውኃ መጠን እንዲቀንሱ የሚያደርጉ ነገሮች የኩላሊት መጎዳትን ያስከትላሉ። በቃጠሎ ምክንያት የተጎዳ ቆዳ ብዙ ውኃ ከሰውነታችን እንዲወጣ ምክንያት ሲሆን ይታያል።
 • በተመሳሳይ የልብ ድካም፣ የጉበት በሽታ፣ የተሰራጨ የደም ኢንፌክሽን ወይም (Sepsis) በደም ስር ያለውን የውኃ መጠን ከደም ስር ወጪ እንዲወጣ በማድረግ የደምን መጠን ሊቀንሱ ይችላሉ።
 • እንዲሁም ወደ ኩላሊት የሚሄደውን ደም የሚቀንሱ የተለያዩ መድኃኒቶች አሉ። ከነዚህ ውስጥ ሽንት የሚያሸኑ መድኃኒቶች ወይም diuretics እንዲሁም እንደ ዳይክሎፌናክ፤ አይቡብሩፌን እና አስፕሪን ያሉ መድኃኒቶች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

 2. በኩላሊት ላይ ቀጥተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ነገሮች

 • የኩላሊት መቆጣት ወይም (Glomerulonephritis)
 • የኩላሊት ኢንፌክሽን
 • ካንሰር 
 • እንደ ካንሰር ሕክምና ወይም ኬሞቴራፒ እና የተለያዩ የ ፀረ ባክቴሪያ ያሉ የተለያዩ መድኃኒቶች
 • ሌላው እንደ ሉፐስ ያሉ በሽታዎች ላይ የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ሥርዓት በራሱ ኩላሊትን ሊያጠቃ ይችላል) 

 3. ሌላው መንሥኤ የሽንት ቧንቧ መዘጋት ነው ( <5%)

ይህም ሽንት ከሰውነት እንዳይወጣ በመከልከል ሽንት ኩላሊት ውስጥ እንዲጠራቀም እና ኩላሊት እንዲጎዳ ያደርጋል። 

ለምሳሌ         

 • የኩላሊት ጠጠር
 • የሆድ፣ የማኅፀን፣ የሽንት ቧንቧ አካባቢ  እጢ\ካንሰር
 • በወንዶች ላይ ደግሞ የፕሮስቴት ችግር

የቆየ የኩላሊት ጉዳት መንሥኤዎች

ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች በዋነኝነት አጣዳፊ የኩላሊት ችግርን የሚያስከትሉ ቢሆኑም በጊዜ ካልታከሙ ግን የቆየ የኩላሊት በሽታን ያስከትላሉ። በተጨማሪም የቆየ የኩላሊት በሽታ የሚያመጡ ነገሮች ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀሱት

 • የስኳር በሽታ
 • የደም ግፊት በሽታ
 • ኤች አይ ቪ ኤድስ እና
 • ሄፕታተስ (የጉበት በሽታ) ናቸው።

ለበለጠ ማብራሪያ ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ።

በቀጣይ የኩላሊት በሽታን እንዴት መከላከል እንደምንችል እናያለን፣ ቸር እንሰንብት።

ተያያዥ ትምህርታዊ ፁሁፎች

Written by Tinsae Zelalem

Blog categories

Disease And Treatment

Fitness and Healthy Diet

Medical Life

Apply for guest writer

 

Share Your Experience With OUR READERS

Membership is Free!

Prerequisites are

– You should be a medical professional

– Post word count should at least be 500

– The blog admin can edit it if necessary.

Comments

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Subscribe to our newsletter to get the latest tips & tricks in your inbox